ክፍል-1 ንብረት ምንድነው?

ንብረት ማለት የሚንቀሳቀስ ወይም የማይንቀሳቀስ ሆኖ በአንድ ግልሰብ፣ ድርጅት፣ ማህበር፣ በህዝብ ወይም በመንግስት ባለቤትነት የተመዘገበ እና ዋጋ ሊያወጣ የሚችል ሀብት ማለት ነው፡፡ ንብረት በብዙ ምድብ እና ዓይነት የሚከፋፈል ሲሆን ለምሳሌ ተንቀሳቃሽ እና የማይንቀሳቀስ፣ አላቂ እና ቋሚ፣ የሚዳሰስ እና የማይዳሰስ ወ.ዘ.ተ በሚባሉ ምድቦች የሚለይ እና በነዚህ ውስጥ በተለያዬ ዘርፍ የሚተነተን ሰፋ ያለ ትርጉም ያለው አርእስት ነው!!የንብረት ግምት ምንድነው?የንብረት ግምት፡- ከላይ ንብረት ምንድነው በሚለው ርእሳችን ስር በጠቀስናቸው የንብረት ዓይነቶች ውስጥ የሚመደብ ሆኖ ይህ ንብረት አንድ የንብረት ገዥ ከሌላ የንብረት ሻጭ ላይ ሁለቱም አካላት የሶስተኛ ወገን ተጽእኖ ሳይደርስባቸው እና ገዥው ስለሚገዛው ንብረት በቂ እውቀት እና ግንዛቤ አግኝቶ ለንብረቱ ሊከፍለው የሚችለው የገንዘብ መጠን ማለት ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ሶስተኛ ወገን የሚለው ንብረት ገዥ ንብረቱን እንዲገዛ ተጽእኖ የሚያሳድርበት አካል (ጉዳይ) ሳይኖርበት (ለምሳሌ፣ ስለንብረቱ የተሳሳተ መረጃ ሳይዝ፣ አለአግባብ የተገኝ ገንዘብን ለመደበቅ ተብሎ የሚደረግ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪን ወ.ዘ.ተ) ሲሆን በገዥ በኩል ንብረቱን እንዲሸጥ ተፅእኖ ሳይኖርበት የሚደረግን ግብይት ለማመልከት ነው (ለምሳሌ፣ ሻጭ ንብረቱን እንዲሸጥ የሚያሰገድደው/የሚገፋፋው ከባቢያዊ ሁኔታ ሳይኖር፣ አስቸኳይ ችግር አጋጥሞት ለችግሩ መፍትሄነት ብቻ በአጭር ጊዜ የሚያደርገው ሽያጭ (በቂ የገበያ ጊዜ ሳያገኝ)፣ ወዘተ ሁኔታዎችን ለማመልከት መሆኑ ግንዛቤ ይወሰድልን፡፡ ስለሆነም የንብረት ግምት የራሱ የሆነ የአሰራር ስርዓት እና የግምት ትንተና ያለው ሂደት ሆኖ አንድ ድርጅት ወይም ግለሰብ ከካሽ (ጥሬ ገንዘብ) ውጭ ያለውን ሃብት/ንብረት በወቅቱ የገበያ ዋጋ መሰረት የንብረቱን መጠን በብር የሚያውቅበት ሙያዊ የስራ ዓይነት ነው፡፡በቀጣይ ክፍል እነዚህን እንመለከታለንየንብረት ግምት ማሰራት ጥቅሙ ምንድነው? የንብረት ግምትን እነማን ያሰራሉ? የንብረት ግምት ዓላማ ምንድነው?የንብረት ግምት አሰራር ዘዴዎች/እንዴት ይሰራል? እነዚህና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች በገጻችን መልስ ያገኛሉ!!

Dear followers, please note that we will post our descriptions with both in English & Amharic.Part-1 English Version—Coming Soon… ገጻችንን ያጋሩልን!! ስለትብብርዎ እናመሰግናለን!! Thank you!